የመቐለው ግብጠባቂ የትጥቅ ድጋፍ አደረገ

የመቐለ 70 እንደርታ ግብጠባቂ ሶፎንያስ ሰይፈ የትጥቅ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።

ላለፉት ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ግብጠባቂው ሶፈንያስ ሰይፈ ሐይራ የስፖርተኞች ማሕበር ኲሓ ሥር ለሚገኙ ከአስራ ሦስት ዓመት በታች ሠላሳ ታዳጊዎች ነው የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች ድጋፍ ያደረገው። ከሠላሳ ሺህ በላይ ወጪ የተደረገበት ይህ ድጋፍ ትጥቅ፣ ኳሶች እና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶች ያካተተ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

በ2009 የውድድር ዓመት አጋማሽ ደደቢትን ለቆ ወደ መቐለ 70 እንደርታ ፈርሞ ክለቡ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ትልቅ ድርሻ የነበረው ይህ ግብ ጠባቂ ከሐይራ ስፖርተኞች ማኅበር ኲሓ ጋር በርካታ ድጋፎች ሲያደርግ መክረሙ ይታወሳል።

የበርካታ እግርኳስ ተጫዋቾች መፍለቅያ የሆነችው ኲሓ ሶፎንያስን ጨምሮ መድሀኔ ታደሰ፣ ወልዳይ ገብረሥላሴ እና ሌሎች ተጫዋቾች የወጡበት አከባቢ ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!