ሽመልስ በቀለ ግብ አስቆጥሯል

ወደ ጥሩ ወቅታዊ ብቃት የተመለሰው ሽመልስ በቀለ ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ጨዋታ ግብ አስቆጥሯል።

በተከታታይ ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ከቆየ በኃላ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ወደ ቋሚነት የተመለሰው ኢትዮጵያዊው የምስር አልመቃሳ አማካይ ሽመልስ በቀለ ቡድኑ ከኢስማዒልያ ባደረገው ጨዋታ በሀምሳ አራተኛው ደቂቃ ግብ አስቆጥሯል። እንግዶቹ ኢስማዒልያዎች በመግዲ አማካኝነት ግብ አስቆጥረው መምራት በጀመሩበት ጨዋታ ባለሜዳዎቹ መቃሳዎች በፓውሊ ቮአቭይ ፣ ሞዲይ ፣ ሽመልስ በቀለ እና ኢብራሂም ባስቆጠርዋቸው አራት ግቦች ታግዘው ከመመራት በመነሳት ጨዋታውን አራት ለአንድ አሸንፈዋል።

በዚ መሰረት በወራጅ ቀጠናው አፋፍ የነበሩት ምስር አልመቃሳዎች ሰባት ደረጃዎች በማሻሻል ከወራጅ ቀጠናው አምልጠዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!