የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ሲጠናቀቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ አቻ ተለያቶ ወደ መሪነቱ ተመልሷል፡፡ ወላይታ ድቻ ከሜዳው ውጪ ድል ቀንቶታል፡፡
በ9፡00 አዲስ አበባ ስታድየም ላይ መከላከያ ወላታ ድቻን አስተናግዶ 2-1 ተሸንፏል፡፡ ወላይታ ድቻ በአላዛር ፋሲካ የ5ኛ ደቂቃ ግብ መምራት ሲችል መከላከያዎች በ26ኛው ደቂቃ በድቻ የግብ ክልል ኳስ በእጅ በመነካቷ ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት መሃመድ ናስር ወደ ግብ በመቀየር አቻ መሆን ችሏል፡፡ የመጀመርያው አጋማሽ የተጠናቀቀውም 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ነው፡፡ ከእረፍት መልስ አምበሉ አላዛር ፋሲካ የወላይታ ድቻን ሁለተኛ ጎል ከመረብ በማሳረፍ ለሶዶው ክለብ 3 ነጥብ አስገኝቷል፡፡ ውጤቱ ወላይታ ድቻን በአንድ ጊዜ 5 ደረጃዎች እንዲያሽሽል ሲያደርገው መከላከያ ወደ 7ኛነት ወርዷል፡፡
በ11፡30 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ በጫታው ቅዱስ ጊዮርጊስ በተለይ በ2ኛው አጋማሽ ግብ ለማግኘት ጫና በመፍጠር ለመጫወት ሲሞክሩ ንግድ ባንኮች በጥልቀት ተከላክለው በመልሶ ማጥቃት በመንቀሳቀስ ውጤት ይዘው ለመውጣት ሞክረዋል፡፡
ይህ ውጤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን 23 አድርሶ ከአዳማ ከተማ ጋር በእኩል ነጥብ በግብ ልዩነት በመብለጥ የሊጉን መሪነት ከ24 ሰአት በኋላ መልሶ ሲረከብ ንግድ ባንክ አንድ ደረጃ ወርዶ 8ኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥ አድርጓል፡፡
የደረጃ ሰንጠረዡ ከ10 ሳምንታት በኋላ ይህንን ይመስላል፡-
የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ