17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት መሪነቱን ሲያስጠብቅ ንግድ ባንክም ድል ቀንቶታል  

 

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን 7ኛ ሳምንት ትላንት በተደረጉ ጨዋታዎች ተጀምሯል፡፡ ዛሬ እና ነገ በሚደረጉ ጨዋታዎችም ይቀጥላል፡፡

3፡00 ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መከላኬን ገጥሞ 2-1 አሸንፏል፡፡ ህያውነህ አመሉ እና አቤል ነጋሽ የንግድ ባንክን ግቦች ከመረብ ሲያሳርፉ አታክልቲ በርሄ የመከላከያን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ውጤቱ ባንክን ከደደቢት በ3 ነጥቦች አንሶ 2ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጦታል፡፡

6፡30 ላይ የሊጉ መሪ ደደቢት ኢትዮጵያ ቡናን ገጥሞ 2-1 አሸንፏል፡፡ የደደቢትን ሁለቱንም ግቦች ዘንድሮ ድንቅ አቋሙን እያሳየ የሚገኘው ዳንኤል ጌድዮን ከመረብ ሰያሳርፍ ታደለ መኮንን የቡናን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል፡፡ ድሉ ደደቢት በ16 ነጥቦች የሊጉን መሪነት እንዲያስጠብቅ አግዞታል፡፡ ጨዋታው እንዲደረግ ፕሮግራም የወጣለት ረፋድ 05፡00 ላይ ቢሆንም ከመጀመርያው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ሌሎች የመዝናኛ ፕሮግራሞች እንዲደረጉ ተደርጎ የደደቢት እና ቡና ጨዋታ 6፡30 ላይ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህም ጨዋታውን ሊከታተል በመጣው ተመልካች ላይ መጉላላትን የፈጠረ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ የሚወጡ ፕሮግራሞች በሰአታቸው የሚደረጉበትን ሁኔታ ቢያመቻች መልካም ነው፡፡

የመካከለኛው ዞን ጨዋታዎች ዛሬ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ በሚደረጉ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ በ9፡00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አፍሮ ጽዮን ፣ በ11፡00 ኤሌክትሪክ ከ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ይጫወታሉ፡፡ ነገ ደግሞ ሐረር ሲቲ ከ አዲስ አበባ ከተማ 11፡00 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል፡-

17

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *