ፌዴሬሽኑ በኢንተርሚደሪ ማኅበር ቅሬታ ቀረበበት

የኢንተርሚደሪ ወይንም የእግር ኳስ ወኪሎች ማኅበር “የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአግባቡ እያስተናገደን ባለመሆኑ ቅሬታችንን ይዘን ወደ ፊፋ ለክስ እናመራለን” ሲሉ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ኢንተርሚደሪ ማኅበር ህጋዊ እውቅናን አግኝቶ መንቀሳቀስ ከጀመረ የወራት ዕድሜን እንዳስቆጠረ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ማኅበሩ እንደ ሌሎች ማኅበራት ሁሉ ህጋዊ እውቅና ተሰቶት የተመሠረተ ቢሆንም ሥራውን በአግባቡ ለመሥራት እክል እየገጠመው እንደሆነ ምክትል ፕሬዝዳንት በረከት ደረጀ ገልጿል።” ሁለት ሦስት ጊዜ ደብዳቤ ልከን እንድንወያይ ጠይቀናል። ይጠሩናል ግን በአግባቡ ሊያስተናግዱን ግን አልቻሉም። ይሄን የስፖርቱ ቤተሰብ እንዲያውቅልን ነው የምንፈልገው። ተጫዋቾች አንድ ጊዜ በኢንተርሚደሪ አማካኝነት መፈረም አለባቸው ይባላል። በሌላ በኩል ደግሞ ያለ ኢንተርሚደሪ መፈረም ይችላሉ እየተባለ የህግ ክፍተት እየታየበት ነው፡፡ ላይሰንስ ሰጥቶ ከመሸኘት የዘለለ ከክለቦች ጋር ህጋዊ ሆነን እንገናኝ ዘንድ መታወቂያ ያስፈልገናል። በቶሎ ጨርሱልን ብንልም ወራትን አስቆጥሮብናል። አባሎቻችንም በአግባቡ ሥራቸውን እየሰሩ አይደለም። ይሄ ደግሞ የእኛ ጥፋት አይደለም። ከአንድ ሁለቴ እንነጋገር ብንላቸውም ነበር ይኸው ሁለት ወራት ስለተቆጠሩ ከእንግዲህ ወደ ፊፋ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል፡፡” ብሏል፡፡

የማኅበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት “የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአግባቡ ባያስተናግደንም ከኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ ከፕሪምየር ሊግ ካምፓኒ እና ከኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች ማኅበር ጋር በጣምራ እየሰራን ነው።” ሲልም አክሏል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!