ኢትዮጵያ ቡና የወሳኝ ተከላካዩን ውል ለረዥም ዓመት አደሰ

የተጫዋቾችን ውል በማራዘም ላይ የተጠመደው ኢትዮጵያ ቡና የወንድሜነህ ደረጄን ውል ለተጨማሪ አራት የውድድር ዓመታት አራዝሟል።

በተቋረጠው የውድድር ዘመን መጀመርያ ባህር ዳር ከተማን ለቆ በሁለት ዓመት ውል ወደ ቡና ያመራው ወንድሜነህ ደረጄ በሊጉ ጎልተው ከወጡ ተጫዋቾች አንዱ የነበረ ሲሆን በቡና አጨዋወት ላይ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች ዋንኛው እንደነበር የሚታወስ ነው። የመሐል ተከላካዩ የመጀመርያ ዓመት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ በቀሪ የአንድ ዓመት ውሉ ላይ ሦስት ዓመት በማከል ከተለመደው የሀገራችን የውል ማራዘም ባሕል በተለየ መልኩ እያራዘሙ በሚገኙት ቡናማዎቹ ቤት እስከ 2016 ድረስ የሚያቆየውን ውል ለማደስ ተስማምቷል።

ቡና በቅርቡ አቡበከር ናስር እና ሚኪያስ መኮንንን እስከ 2017 እና አማኑኤል ዮሐንስን እስከ 2016 የሚያቆይ ውል ማደሱ የሚታወስ ነው።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!