ለቀድሞ ተጫዋች የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

የኢትዮጵያ ተጫዋች ማኅበር ለቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ ተጫዋች ተስፋሁን ጋዲሳ (ኮል) የድጋፍ ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያ ቡና፣ በተለያዩ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች እና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በየመን ሊግ በመጫወት በዘጠናዎቹ ከፍተኛ ዝና እና ተወዳጅነት ያተረፈው አመለሸጋው ተስፋሁን ጋዲሳ (ኮል) በአሁኑ ሰዓት ከባለቤቱ እና ከሁለት ልጆቹ ጋር በርዕስ በዕርስ ጦርነት በምትታመሰው የመን ይገኛል። ተጫዋቹ ወደ ትውልድ ሀገሩ ለመመለስ ስለሚፈልግ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች አጠቃላይ የስፖርት ቤተሰቦች ድጋፍ ያስፈልገዋል። በዚህም የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኀበር በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ድጋፍ እንድታደርጉለት ማኀበሩ ጥሪውን አቅርቧል።

ለተስፋሁን ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1000299142788© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!