ሴቶች ፕሪምየር ሊግ| ድሬዳዋ ከተማ የአሰልጣኟን ውል አራዘመ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተካፋይ የሆነው ድሬዳዋ ከተማ የአሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩን ውል አድሷል፡፡

ድሬዳዋ በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዓመት በዘጠኝ የሊጉ ጨዋታዎች ስድስተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ ይገኝ የነበረ ሲሆን ቡድኑን በአሰልጣኝነት ያለፉትን ሁለት ዓመታት ስትመራ የነበረችው አሰልጣኝ ብዙዓየሁ ጀምበሩ ነች፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ክለቡን ከተረከበች በኃላ ጥሩ ቡድን የሰራች ሲሆን ክለቡም ውሏ መጠናቀቁን ተከትሎ ተጨማሪ አንድ ዓመትን እንድትቆይ ውሏ ተራዝሞላታል፡፡

አሰልጣኝ ብዙአየሁ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፀችው ጠንካራ እና ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት ክለቡ ከሰሞኑ ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚገባ ገልፃለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!