ኢትዮጵያ ቡና ከሐበሻ ቢራ ጋር የስፖንሰርሺፕ ውል አደሰ

ሐበሻ ቢራ ኢትዮጵያ ቡናን ለ2013 የስፖንሰርሺፕ ስምምነቱን ማደሱን አሁን እየተሰጠ በሚገኘው መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

ከሐምሌ አንድ ቀን 2012 የጀመረው አዲሱ ስምምነት እስከ ሰኔ 30/2013 ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን ሐበሻ ቢራ በአጠቃላይ 28 ሚሊዮን 250 ሺ ብር ለስፖንሰር ሺፕ ይከፍላል።

ከአጠቃላይ 28 ሚ 250 ሺ ብር ውስጥ 18 ሚሊዮን በቀጥታ ስፖንሰር ሺፕ፣ 2 ሚልየን በዓመት ውስጥ ቡና ለሚያዘጋጃቸው 4 ዝግጅቶች፣ 4.5 ሚልየን ለደጋፊዎች ማሊያ፣ 3.75 ሚልየን ብር ለ2013 የቡና ቤተሰብ ሩጫ እንዲሁም ለተጫዋቾች ኢንሴንቲቭ የሚሰጥ ገንዘብም በውሉ ተቀምጧል።

ዝርዝር መረጃዎች ከቆይታ በኋላ ይቀርባሉ
© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!