ሁሉም ጨዋታዎች ተጠናቀዋል፡፡ ውጤቶቹ ይህንን ይመስላሉ፡፡
ሲዳማ ቡና 2-2 ደደቢት (14′ 16′ ፍጹም ተፈሪ : 75′ ሳምሶን ጥላሁን, 90+2′ ብርሃኑ ቦጋለ)
ሀዋሳ ከተማ 3-1 አርባምንጭ ከተማ (12′ እስራኤል እሸቱ, 17′ አስቻለው ግርማ, 24′ ደስታ ዮሃንስ : 71′ ታገል አበበ)
ድሬዳዋ ከተማ 1-1 ኢትዮጵያ ቡና (79′ ፍቃዱ ወርቁ : 34′ ዊልያም ያቤውን)
ሀዲያ ሆሳዕና 0-1 ኤሌክትሪክ (68′ ፒተር ኑዋድኬ)
ተጠናቀቀ
ይርጋለም ፡ በሲዳማ ቡና እና ደደቢት መካከል የተደረገው ጨዋታ 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቀቀ፡፡
ይርጋለም ፡ ጎልልል!!! ደደቢት
90+2′ ብርሃኑ ቦጋለ ከማእዘን የተሸገረውን ኳስ ተጠቅሞ ደደቢትን አቻ አድርጓል፡፡
ተጠናቀቀ
ድሬዳዋ ፡ በድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና መካከል የተደረገው ጨዋታ 1-1 ተጠናቀቀ፡፡
ተጠናቀቀ
ሆሳዕና ፡ በሀዲያ ሆሳዕና እና ኤሌክትሪክ መካከል የተደረገው ጨዋታ በኤሌክትሪክ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
ተጠናቀቀ
ሀዋሳ ፡ በሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል የተደረገው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 3-1 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡
ይርጋለም ፡ 82′ ዳዊት ፍቃዱ ከመስመር የተሸገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ገባ ተብሎ ሲጠበቅ ነጥሮ የግቡን አግዳሚ ታኮ ወጥቷል፡፡ ደደቢት የአቻነት ጎል ፍለጋ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ድሬዳዋ ጎልልል!!! ድሬዳዋ ከተማ
79′ ፍቃዱ ወርቁ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ድሬዳዋ ከተማን አቻ አድርጓል፡፡
ድሬዳዋ 76′ ኢትዮጵያ ቡና ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ አግኝቶ ኤልያስ ማሞ አምክኖታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ድሬዳዋ ከተማዎች በጥሩ መልሶ ማጥቃት በበላይ አባይነህ አማካኝነት ቢሞክሩም የግቡ ቋሚ መልሶባቸዋል፡፡
ይርጋለም : ጎልልል!!! ደደቢት
75′ ሳምሶን ጥላሁን የተገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡ ሲዳማ 2-1 ደደቢት
ይርጋለም ፡ 74′ ዳዊት ፍቃዱ ላይ ጥፋት መሰራቱን ተከትሎ ለደደቢት የፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቷል፡፡
ድሬዳዋ ፡ 67‘ ኤልያስ ማሞ በግንባሩ ገጭቶ የሞከራት ኳስ የግቡን አግዳሚ ለትማ ወጥታለች፡፡ ጨዋታው በቡና 1-0 መሪነት ቀጥሏል፡፡
ሀዋሳ ፡ ጎልልል!!! አርባምንጭ ከተማ
71′ አርባምንጭ ከተማ ተቀይሮ በገባው ታገል አበበ በአማካኝነት ግብ አስቆጥሯል፡፡
ሆሳዕና : ጎልልል!!! ኤሌክትሪክ
ፒተር ኑዋድኬ በ68ኛው ደቂቃ ኤሌክትሪክን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ሀዋሳ ፡ 60′ ሀዋሳ በ2ኛው አጋማሽም በአርባምንጭ ላይ የእንቅስቃሴ ብልጫ እየወሰደ ነው፡፡ ታፈሰ ሰለሞን ድንቅ እንቅስቃሴ በማሳየት ከተመልካቹ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል፡፡
ይርጋለም : 51′ ዳዊት ከሳሚ ሳኑሚ ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ ጥሩ የግብ ማግባት አጋጣሚ ቢያገኝም ሚዛኑን ስቶ ወድቋል፡፡ ዳዊት ጥፋት እንደተሰራበት በመግለፅ የፍፁም ቅጣት ምት ይገባኛል በማለት ከአርቢቴር በአምላክ ተሰማ ላይ ቅሬታ እያሰማ ይገኛል፡፡
ሆሳዕና ፡ 58′ ኤሌክትሪክ በ2ኛው አጋማሽ በተሸለ ሁኔታ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
10፡10 ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታ 2ኛ አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
10:10 የሲዳማ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ 2ኛ አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
10:05 የሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 2ኛ አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
10:00 የሀዲያ ሆሳዕና እና ኤሌክትሪክ ጨዋታ 2ኛ አጋማሽ ተጀመረ፡፡
09፡57 የሲዳማ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ በሲዳማ ቡና 2-0 መሪነት የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ይርጋለም ፡ የጨዋታው 45 ደቂቃ ተጠናቆ 4ኛ ዳኛው ተጨማሪ 3 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡
09፡52 ድሬዳዋ ላይ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 1-0 እየመራ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
09፡50 ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ አርባምንጭን 3-0 እየመራ የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
09፡45 ሆሳዕና ላይ ሆሳዕና ከተማ ከኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታ ካለግብ የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ድሬዳዋ ፡ 34′ ጎልልል!!! ኢትዮጵያ ቡና
ዊልያም ያቤውን በራሱ ጥረት ከመስመር በማጥበብ ወደ ግብ የላከው ኳስ ኢትዮጵያ ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡ አስቆጠረ፡፡ ድሬዳዋ ከተማ 0-1 ኢትዮጵያ ቡና
09:35 በሆሳዕና አቢዮ አርሳሞ ስታድየም ሆሳዕና ከኤሌክትሪክ ካለግብ 35 ደቂቃ ደርሰዋል፡፡ ሀዋሳ ላይ 38 ደቂቃዎች የተቆጠሩ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ 3-0 እየመራ ይገኛል፡፡ ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና ካለግብ 30 ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡
ሀዋሳ ፡ 24′ ጎልልል!!! ሀዋሳ ከተማ
ደስታ ዮሃንስ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስት በግራ እግሩ አክርሮ የመታው ኳስ ከመረብ አርፏል፡፡ 3-0
ሀዋሳ ፡ 17′ ጎልልል!!! ሀዋሳ ከተማ
አስቻለው ግርማ ከደስታ ዮሃንስ የተሸገረለትን ኳስ ወደ ግብነት ቀይሮ ሀዋሳ ከተማ ከ20 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ 2-0 እንዲመራ አስችሏል፡፡
ይርጋለም 16′ ጎልልል!!!!! ሲዳማ ቡና
ፍጹም ተፈሪ ከማዕዘን ምት የተሸገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ለራሱ እና ለቡድኑ 2ኛውን ግብ አስጠቆረ፡፡
ይርጋለም 14 ‘ ጎልልል!!!!! ሲዳማ ቡና
አዲስ ግደይ ከመስመር ያሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ፍጹም ተፈሪ ሲዳማ ቡናን ቀዳሚ አድርጓል፡፡
ይርጋለም 8′ ከቅጣት ምት የተሸገረውን ኳስ ስዩም ሞክሮ ለአለም አድኖበታል
ይርጋለም 6′ ሳውሬል በግራ መስመር ስዩምን አልፎ ወደ ግብ የመታው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
ሀዋሳ : 12′ ጎልልል!!!! ሀዋሳ ከተማ
እስራኤል እሸቱ ሀዋሳ ከተማን ቀዳሚ ያደረገች ግብ በ12ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡
ሁሉም ጨዋታ ተጀምሯል፡፡ የሲዳማ ቡና እና የደደቢትን ጨዋታ በዋነኝነት እያስተላለፍን የሌሎቹን ጨዋታዎች ዋና ዋና ሁነቶች በመሃል በመሃል እንዘግብላችኋለን፡፡
09፡10 የሲዳማ ቡና እና የደደቢት ጨዋታ ተጀምሯል
09፡06 የድሬዳዋ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ተጀምሯል
08:58 የሀዲያ ሆሳዕና እና ኤሌክትሪክ ጨዋታ ተጀምሯል፡፡
09፡00 የሀዋሳ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ተጀምሯል
ሀዲያ ሆሳዕና ከ ኤሌክትሪክ
የሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ
ሀብታሙ ከድር
ውብሸት አለማየሁ – ታረቀኝ – ቢንያም ገመቹ – ሄኖክ አርፊጮ
መብራቱ ገብረስላሴ – አድናን ቃሲም – አበባየሁ ዮሃንስ – አምራላ ደልቻታ – ዱላ ሙላቱ
ተዘራ አቡቴ
የኤሌክትሪክ አሰላለፍ
አሰግድ አክሊሉ
አወት ገ/ሚካኤል – አልሳዲቅ አልማሂ – ሲሴይ ሃሰን – አማረ በቀለ
በሃይሉ ተሻገር – ደረጄ ኃይሉ – አሸናፊ ሽብሩ – አብዱልሃኪም ሱልጣን
ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ
ሲዳማ ቡና ከ ደደቢት
የሲዳማ ቡና አሰላለፍ
ለአለም ብርሃኑ
ዘነበ ከበደ – አንተነህ ተስፋዬ – አወል አብደላ – ሳውሬል ኦልሪሽ
አዲስ ግደይ – ሙሉአለም መስፍን – አሳምነው አንጀሎ – ፍፁም ተፈሪ – አዲስ ደበበ
ኤሪክ ሙራንዳ
የደደቢት አሰላለፍ
ታሪክ ጌትነት
ስዩም ተስፋዬ – አይናለም ኃይለ – አክሊሉ አየነው – ተካልኝ ደጀኔ
ሽመክት ጉግሳ – ያሬድ ዝናቡ – ሳምሶን ጥላሁን – ብርሃኑ ቦጋለ
ሳሚ ሳኑሚ – ዳዊት ፍቃዱ
ሀዋሳ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
የሀዋሳ ከተማ አሰላለፍ
ብሪያን ቶቤጎ
ዳንኤል ደርቤ – ሙጂብ ቃሲም – ግርማ በቀለ – ደስታ ዮሃንስ
ሙሉጌታ ምህረት – ኃይማኖት ወርቁ
ጋዲሳ መብራቴ – ታፈሰ ሰለሞን – አስቻለው ግርማ
እስራኤል እሸቱ
የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ
መሳይ አያኖ
ፀጋዬ አበራ – በረከት ቦጋለ – አበበ ጥላሁን – ወርቅይታደል አበበ
ምንተስኖት አበራ – ትርታዬ ደመቀ – አማኑኤል ጎበና – ታደለ መንገሻ
በረከት ወልደፃዲቅ – ተሾመ ታደሰ
ድሬዳዋ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና
የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ
ሳምሶን አሰፋ
አብዱልፈታህ ከማል – ተስፋዬ ዲባባ – ብርሃኑ ሆራ – ሄኖክ አዱኛ
ዳዊት እስጢፋኖስ – ይሁን እንደሻው – ዮናስ ገረመው
አክሌስያ ግርማ – ፍቃዱ ታደሰ – በላይ አባይነህ
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ሀሪሰን ሀውሲ
አብዱልከሪም መሃመድ – ኤፍሬም ወንድወሰን – ሳላምላክ ተገኝ
ኤልያስ ማሞ – ጋቶች ፓኖም – መስኡድ መሃመድ
ጥላሁን ወልዴ – ዊልያም ያቤውን – እያሱ ታምሩ