ያሬድ ታደሰ ወደ ወልቂጤ ከተማ አምርቷል

ለሰበታ ከተማ ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረው ያሬድ ታደሰ በይፋ የወልቂጤ ከተማ ተጫዋች ሆኗል፡፡

በዝውውር መስኮቱ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ለማስፈረም ሲስማሙ የነበሩት ወልቂጤ ከተማዎች በትናንትናው ዕለት ባዬ ገዛኸኝን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡ ሆኖም ክለቡ ራሱን ለማጠናከር ተጨማሪ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን ቀጥሎ የመስመር አጥቂ እና የመሀል አማካይ ሥፍራ ላይ መጫወት የሚችለው ያሬድ ታደሰን በሁለት ዓመት የውል ኮንትራት ፌዴሬሽን በመገኘት አስፈርሟል፡፡ ያሬድ መስኮቱ ከመከፈቱ በፊት ለሰበታ ከተማ ለመጫወት ተስማምቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ቢኒያም በላይ ተጫውቶ ባለፈበት የድሬዳዋው ዋልያ ክለብ ውስጥ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ያሬድ የከፍተኛ ሊግ ክለብ ተሳታፊ የነበረው እና በአሁኑ ሰዓት በፈረሰው ናሽናል ሲሜንት ከቢ ቡድን እስከ ዋናው ድረስ ተጫውቶ ያሳለፈ ሲሆን ከ2010 ጀምሮ ለትውልድ ከተማው የፕሪምየር ሊጉ ተሳታፊ ድሬዳዋ ከተማ ሲጫወት ቆይቷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!