ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ድሬዳዋ ከተማ የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ውል አደሰ

ድሬዳዋ ከተማዎች የስድስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት አራዝመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተሳታፊ የሆኑት ድሬዳዋ ከተማዎች ከሰሞኑ የአሰልጣኟን ብዙዓየሁ ጀምበሩን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም ውላቸው የተጠናቀቀ ተጫዋቾችን ማራዘም ቀዳሚው የክለቡ ተግባር ሆኗል፡ በዚህም መሠረት በክለቡ የነበሩ ስድስት ተጫዋቾች ኮንትራታቸው ተራዝሟል፡፡ ሂሩት ደሴ (ግብ ጠባቂ)፣ አያንቱ ውብዓየሁ (ተከላካይ)፣ አያን ሙሳ እና ዕድላዊት ተመስገን (አማካዮች)፣ ሊና መሐመድ እና ቤተልሄም ኪዳኔ (አጥቂዎች) ለተጨማሪ ዓመት ውል ያራዘሙ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

ውል ካደሱ ተጫዋቾች መካከል በተሰረዘው የውድድር ዓመት የወንድ ቡድኑ ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ተሹሞ የነበረው እዮብ ተዋበ የሴት ቡድኑ ረዳት ተደርጎ ተመድቧል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!