ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | መቐለ 70 እንደርታ አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ባለፈው ሳምንት የአስራ ሰባት ተጫዋቾችን ውል ያደሱት መቐለ 70 እንደርታዎች በዛሬው ዕለት አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

ለመቐለ 70 እንደርታ በ2011 ስትጫወት የነበረችውና ዓምና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ያሳለፈችው ታዳጊዋ ግብ ጠባቂ መሠረት ተፈራ ከፈረሙት መካከል አንዷ ስትሆን በሲዳማ ቡና፣ ዳሽን ቢራ፣ መከላከያ እና የተሰረዘውን የውድድር ዓመት ለጌዲኦ ዲላ አምበል እና የመሐል ተከላካይ በመሆን ስትጫወት የቆየችሁ ፋሲካ በቀለ ሌላኜዋ ፈራሚ ናት። በዳሽን ቢራ እና ያለፉትን ሦስት ዓመታት ለመከላከያ ስትጫወት የነበረችው አጥቂዋ ሄለን እሸቱ ሦስተኛዋ ፈራሚ ስትሆን የኢትዮጵያ ወጣቶች እና ስፖርት አካዳሚ ፍሬ የሆነችውና በቅዱስ ጊዮርጊስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በመጫወት ያሳለፈችው አማካይ ብርሀን ገብረሥላሴ እና የቀድሞዋ የመከላከያ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ያሳለፈችው የመስመር አጥቂ አክበረት ገብረፃድቅ በዛሬው ዕለት የፈረሙ ሌሎች አዳዲስ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!