ኢትዮጵያ ቡናዎች ከነገ ጀምሮ ወደ ዝግጅት ይገባሉ

ኢትዮጵያ ቡናዎች ቅዳሜ የ2013 ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ፡፡

አዲስ የውል አሰራርን ለተጫዋቾች በማቅረብ የረጅም ጊዜ ኮንትራት በመስጠት ብቅ ያሉት የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ኢትዮጵያ ቡናዎች በክረምቱ አቤል ማሞ፣ አበበ ጥላሁን እና ዘካሪያስ ቱጂን በአዲስ ዝውውር ሲያስፈርሙ የወሳኝ ተጫዋቾቹንም ውል ማራዘማቸው ይታወሳል፡፡ ክለቡ ከሰሞኑ ተጫዋቾቹ ወደ ካምፕ እንዲገቡ ካደረገ በኃላ የሜዲካል እና የኮቪድ 19 ምርመራን አጠናቆ ሁሉም ተጫዋቾች ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ ከነገ ማለዳ ጀምሮ መቀመጫቸውን ለቡ አድርገው የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በሜዳቸው ይጀምራሉ፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ከመቐለ 70 እንደርታ፣ ፋሲል ከነማ፣ ሲዳማ ቡና እና ባህር ዳር ዳር ከተማ ቀጥሎ ወደ ዝግጅት የሚገባ አምስተኛ ክለብም ሆኗል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!