ሰበታ ከተማ አጥቂ አስፈረመ

ከሀዋሳ ከተማ ጋር ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረው አጥቂ ለሰበታ ከተማ ፈረመ፡፡

በያዝነው ሳምንት አዲስ አሰልጣኝ እንደሚቀጥሩ የሚጠበቁት ሰበታ ከተማዎች በዛሬው ዕለት አጥቂው እስራኤል እሸቱን አስፈርመዋል፡፡ ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኃላ ያለፉትን አራት ዓመታት በዋናው ቡድን ሲጫወት የነበረው ይህ ፈጣን አጥቂ ከአንድ ወር በፊት በልጅነት ክለቡ ለአንድ ተጨማሪ ዓመት ውሉን ለማደስ ቅድመ ስምምነት ፈፅሞ የነበረ ቢሆንም ከሰዓታት በፊት በፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት ተገኝቶ የአንድ ዓመት ውል በመፈረም የሰበታ ከተማ ተጫዋች መሆኑ እርግጥ ሆኗል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!