መስፍን ታፈሰ ነገ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል

በኢኳቶርያል ጊኒ በሙከራ ላይ የሚገኘው መስፍን ታፈሰ ነገ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል።

ባለፈው ወር ወደ ኢኳቶርያል ጊኒው ቻምፒዮን ፉትሮ ኪንግስ ለሙከራ ያቀናው የሀዋሳ ከተማው አጥቂ መስፍን ታፈሰ ዛሬ ሌሊት ኢትዮጵያ ገብቶ ነገ ጠዋት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚያደርግ ሲሆን ውጤቱ ታይቶ ብሔራዊ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሏል።

ላለፈው አንድ ወር ከፉትሮ ኪንግስ ጋር ልምምድ ሲሰራ የቆየው መስፍን ቡድኑ ባደረጋቸው የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ አድርጓል። ተጫዋቹ ከብሄራዊ ቡድን መልስ ከኢኳቶርያል ጊኒው ክለብ ጋር ጉዳይ እንደሚለይለት ታውቋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!