ድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቾቹን ጠርቷል

ድሬዳዋ ከተማዎች የ2013 ቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የሚጀምሩበት ጊዜ ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተወዳዳሪው ድሬዳዋ ከተማ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከከፍተኛ ሊጉ እስከ ፕሪምየር ሊግ ያሉ ተጫዋቾችን ተመልክቶ ያስፈረመ ሲሆን ረዳት አሰልጣኞችንም በመሾም ለአዲሱ ዓመት ራሳቸውን ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ደግሞ ቅድመ ውድድር ዝግጅትን ለማድረግ ለተጫዋቾቹ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ሁሉም ተጫዋቾች ነገ ወደ ድሬዳዋ አምርተው ክሊኦፓትራ በተባለ ሆቴል ካረፉ በኃላ የኮቪድ 19 ምርመራ የሚደረግላቸው ሲሆን የህክምናውን ውጤት ተከትሎ ሐሙስ ዕለት የ2013 የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እንደሚጀምሩ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!