አንድ ተጫዋች በግል ጉዳይ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ውጭ ሆነ

ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ውበቱ አስር ተጫዋቾች ቀንሰው 26 ተጫዋቾቻቸውን አሰውቀው የነበረ ቢሆንም አንድ ተጫዋች በግል ጉዳይ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድኑ ውጭ መሆኑን ታውቋል።

በአዳማ ከተማ የእግርኳስ ጅማሬውን ያደረገው እና በዚህ ዓመት ዐፄዎቹን የተቀላቀለው የመስመር አጥቂው በረከት ደስታ የግል ጉዳይ አጋጥሞት ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ከተነጋገረ በኃላ በስምምነት ከቡድኑ ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል።

የበረከት መውጣትን ተከትሎ በ25 ተጫዋቾች ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ብሔራዊ ቡድኑ የፊታችን ዓርብ ሽመልስ በቀለን የሚያገኝ ሲሆን በኒጀሩ ጨዋታ መዳረሻ አራት ተጫዋቾች ከዋልያዎቹ አሰላለፍ ይቀነሳሉ ተብሎም ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!