ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ፡ በትላንት እና ዛሬ ጨዋታዎች ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሐረር ሲቲ እና ኤሌክትሪክ አሸንፈዋል

በኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ መካከለኛ ዞን 7ኛ ሳምንት ትላንት እና ዛሬ በተካሄዱት ጨዋታዎች ሐረር ሲቲ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ አና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ትላንት 09፡00 ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ አፍሮጽዮንን ገጥሞ 2-1 አሸንፏል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግቦች ሎክ ፓውሊንሆ እና ተስፋዬ በቀለ ሲያስቆጥሩ ፈይሰል ዲኖ የአፍሮ ጽዮንን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ድሉ ቅዱስ ጊዮርጊስን 4ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጠው ሲያስጠጋው አፍሮ ፅዮን በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ እንዲገደብ አድርጎታል፡፡

በ11፡00 ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን 2-0 አሸንፏል፡፡ የኤሌክትሪክን የድል ግቦች ከመረብ ያሳረፉት በለጠ መሃመድ እና ካሊድ መሃመድ ናቸው፡፡ ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገበው ኤሌክትሪክ ከደደቢት በ2 ነጥቦች አንሶ 2ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል በጥሩ አጀማመሩ መዝለቅ ያልቻለው ወጣቶች አካዳሚ በተከታታይ ሽንፈቶች አስተናግዶ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ዛሬ 11፡00 ላይ ሐረር ሲቲ አዲስ አበባ ከተማን ገጥሞ 2-0 አሸንፏል፡፡ የሐረር ሲቲን ሁለቱንም የአሸናፊነት ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ታዲዮስ አዱኛ ነው፡፡ ሐረር ሲቲ ደረጃውን ወደ 5ኛ ሲያሻሽል አዲስ አበባ ከተማ ባለበት 8ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል፡፡

በአጠቃላይ በ7ኛ ሳምንት የተደረጉት ጨዋታዎች ይህንን ይመስላሉ፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2-1 መከላከያ

ደደቢት 2-1 ኢትዮጵያ ቡና

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 አፍሮ ፅዮን

ኤሌክትሪክ 2-0 ኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ

ሐረር ሲቲ 2-0 አዲስ አበባ ከተማ

የደረጃ ሰንጠረዥ

17 PL

ቀጣይ ጨዋታዎች

(ሁሉም ጨዋታዎች በአአ ስታድየም ይደረጋሉ)

ቅዳሜ 19/06/2008

09፡00 የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ከ ደደቢት

11፡00 አፍሮ ጽዮን ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

እሁድ 20/06/2008

03፡00 ኤሌክትሪክ ከ ሐረር ሲቲ

05፡00 አአ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሰኞ 21/06/2008

09፡00 መከላከያ ከ ኢትዮጵያ ቡና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *