ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የነባሮችንም ውል አድሷል

ቡታጅራ ከተማ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአስራ ስድስት ነባሮችን ውል አራዝሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ቡታጅራ ከተማ በቅርቡ ዋና አሰልጣኝ በማድረግ ካሊድ መሐመድን ከቀጠረ በኃላ የዝውውር መስኮቱን በመቀላቀል ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። የአጥቂ መስመር ተጫዋቾቹ ክንዴ አቡቹ (ከዲላ ከተማ) እና ሙሴ እንዳለ (ከካፋ ቡና) አዲሶቹ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

ውል ያራዘሙ ነባር ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው:-

ፋሪስ አላዊ፣ ሚስባህ ህያር፣ ረሂሙ ዑስማን፣ ሱራፌል ገዙ፣ ኤርሚያስ ለብሬ፣ ሚፍታህ መሐመድ፣ በጋሻው ክንዴ፣ ዕያዩ ሲሳይ፣ ሙፊድ አንድሪስ፣ ነፃነት ወርቁ፣ አብርሀም ወርቁ፣ ሱራፌል ከድር፣ አማኑኤል ቦርባ፣ ፀጋ ማቲዮስ፣ አቤል ሽጉጤ እና ተስፋዬ ባንተይርጋ

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!