ከፍተኛ ሊግ | ለገጣፎ ለገዳዲ የአሰልጣኙን ውል አራዘመ

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተወዳዳሪው ለገጣፎ ለገዳዲ የዋና እና ምክትል አሰልጣኞቹን ውል ማሬዘሙ ታውቋል።

ለገጣፎ በ2011 ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማለፍ እስከመጨረሻው ሳምንት ድረስ ሲፎካከር እንደቆየ የሚታወቅ ሲሆን በ2012 ውድድሩ እስተቋረጠበት ጊዜ ድረስም ጥሩ ጉዞ ካደረጉት ቡድኖች መካከል ይጠቀሳል። ይህን ጥንካሬውን ይዞ ለመዝለቅም የዳዊት ሀብታሙ እና ምክትሎቹን ውል አድሷል። ለደሴ ከተማ አሰልጣኝነት እስከመጨረሻ እጩ ውስጥ መጓዝ የቻለው ወጣቱ አሰልጣኝ በቀጣይ የተጫዋቾችን ውል በማስ እና አዳዲሶችን ወደ ቡድኑ በመቀላቀል ወደ ዝግጅት የሚገባ መሆኑን ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

ለገጣፎ ከዋና አሰልጣኙ በተጨማሪ ምክትሉ ጥላሁን ተሾመ እና የጎል ጠባቂዎች አሰልጣኙ ፍቅዱ ገብሩን ውልም አድሷል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!