ከፍተኛ ሊግ | ጋሞ ጨንቻ ሦስት ተጨማሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ እየተወዳደረ የሚገኘው ጋሞ ጨንቻ ሦስት ተጨማሪ ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ አካቷል፡፡

የከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ጠንካራ ተፎካካሪ ጋሞ ጨንቻ በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ እየተመራ በርካታ አዳዲስ እንዲሁም ነባር ተጫዋቾቹን በማስፈረም ተጠምዶ የሰነበተ ሲሆን አሁን ደግሞ ነጋ ከበደ (ግብ ጠባቂ ከአርሲ ነገሌ)፣ ኪሩቤል ፍቅረማርቆስ (ከጂንካ ከተማ የመሀል ተከላካይ) እና ዳዊት ዳና (ከሶዶ ከተማ የተከላካይ አማካይ) አስፈርሟል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!