ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሁለት ተጫዋቾቹን ውል አራዝሟል

ከታችኛው ቡድን ወደ ዋናው አድገው አሳዳጊያቸውን በማገልገል የቆዩ ሁለት አማካዮች ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይቆያሉ

ለቀጣይ የውድድር ዓመት አዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ቡድናቸው ለማጠናከር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚሰለጥኑት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን ደግሞ የሁለት የታዳጊ ቡድናቸው ፍሬ የሆሙት አንዋር በድሩ እና ሄኖክ ገብረህይወትን ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።

አንዋርም ሆነ ሄኖክ ከታችኛው የኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡድን ተገኝተው ባለፉት ሁለት ዓመታት ቡድኑን በጥሩ ሁኔታ ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን አሁን ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በአሳዳጊያቸው ቤት ለመቆየት ውላቸውን ማራዘማቸው ታውቋል።