ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሀምራዊ ለባሾቹ ጋር ቆይታ የነበረው አማካይ ውሉን ለማራዘም ተስማምቷል

ከሰዓታት በፊት የጫላ ተሺታ እና የእዮብ አለማየሁን ዝውውር ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች አሁን ደግሞ የአማካዩ ዘላለም አበበን ውል ማራዘማቸው ታውቋል። ከሁለት ዓመት በፊት ከከፍተኛ ሊጉ ጅማ አባ ቡና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የተቀላቀለው ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ29 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2291 ደቂቃዎች ሜዳ ላይ ቆይታ በማድረግ አንድ ጎል በማስቆጠር ጥሩ የውድድር ዓመት ሲያሳለፍ አሁን ደግሞ ለሁለት ዓመታት ውሉን ማራዘሙ እርግጥ ሆኗል።

