እዮብ አለማየሁ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀላቀለ

እዮብ አለማየሁ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተቀላቀለ

ወልዋሎን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረ ተጫዋች ወደ ሀምራዊ ለባሾቹ አመራ

ከሳምንታት በፊት ወደ ወልዋሎ ለማምራት ከስምምነት ደርሶ የነበረው የፊት መስመር ተጫዋቹ እዮብ አለማየሁ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል። የቢጫዎቹ የክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጀመርያ ፈራሚ ለመሆን ከስምምነት ደርሶ የነበረው ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት ወደ ሀምራዊ ለባሾቹ ለማምራት ከስምምነት የደረሰ ሲሆን በቅርቡ ፌርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

በወላይታ ድቻ ታዳጊ ቡድን ፍሬ የሆነው እዮብ በ2008 ወደ ዋናው ቡድን አድጎ አሳዳጊ ክለቡን ካገለገለ በኋላ በጅማ አባጅፋር ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና መጫወቱ የሚታወስ ነው።