ሀምራዊ ለባሾቹ የመስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

ሀምራዊ ለባሾቹ የመስመር ተጫዋች አስፈርመዋል

ያለፉት ዓመታት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታ የነበረው ጫላ ተሺታ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምርቷል

በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ከቡድኑ በለለቀቁ ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን ለማምጣት በዝውውሩ ተሳትፎ እያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ፈጣኑን የመስመር አጥቂ ጫላ ተሺታን ማስፈረማቸውን አውቀናል።

በሻሸመኔ ከተማ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው እና በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡደን ባሳየው አስደናቂ ብቃት እራሱን ማስተዋወቅ የቻለው ጫላ ባለፉት ዓመታት በሲዳማ ቡና ፣ ወልቂጤ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ሀድያ ሆሳዕና ማሳለፉ ሲታወስ አሁን ደግሞ በሁለት ዓመት ውል መዳረሻው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል።