ከፍተኛ ሊግ | ለገጣፎ ለገዳዲ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የአሰልጣኞቹን ውል በቅርቡ ያደሰው ለገጣፎ ለገዳዲ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ አካቷል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሀ ጠንካራ ከሚባሉ የምድቡ ጠንካራ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው ለገጣፎ ለገዳዲ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት የአሰልጣኝ ደዊት ሀብታሙን እንዲሁም የረዳቶቹን ኮንትራት ከሰሞኑ ካደሰ በኃላ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ማስፈረሙ ገብቷል፡፡ በዚህም መሠረት በሽር ደሊል (ግብ ጠባቂ ከስልጤ ወራቤ)፣ ብሩክ እንዳለ (አማካይ ከገላን ከተማ) እና ሀብታሙ ፈቀደ (የመስመር አጥቂ ከገላን ከተማ) ፈርመዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!