ፋሲል ከነማ ከ ዩኤስ ሞናስቲር: የዐፄዎቹ አሰላለፍ

ፋሲል ከነማ በዛሬው ዕለት ከቱኒዚያው ዩኤስ ሞናስቲር ጋር ለሚያርገው ጨዋታ የሚጠቀምበት አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ ወደ ሞናስቲር አቅንቶ 2-0 ከተሸነፈው ስብስብ አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ ያደረጉ ሲሆን ይሁን እንደሻው እና ሳሙኤል ዮሐንስ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጠው በዛብህ መለዮ እና አምሳሉ ጥላሁን በመጀመርያ አሰላለፍ ተካተዋል። 

የፋሲል አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ሚኬል ሳማኬ

ሰዒድ ሀሰን – ከድር ኩሊባሊ- ያሬድ ባየህ – አምሳሉ ጥላሁን

ሀብታሙ ተከስተ

ሽመክት ጉግሳ – ሱራፌል ዳኛቸው – በዛብህ መለዮ –  በረከት ደስታ

ሙጂብ ቃሲም

ጨዋታው 10:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚጀምር ሲሆን ሩዋንዳዊያን ዳኞች ጨዋታውን ይመሩታል። 

© ሶከር ኢትዮጵያ