​ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አዳማ ከተማ አዲስ ተጫዋች ሲያስፈርም የአማካይዋን ውል አራዘመ

አዳማ ከተማ ሁለገቧን ተጫዋች ሄለን ሰይፉን ሲያስፈርም የአማካይዋ ፋሲካ መስፍንን ውልም አድሷል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው አዳማ ከተማ ከወራት በፊት የአሰልጣኝ ሳሙኤል አበራን ውል ካራዘመ በኃላ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ የቀላቀለ ሲሆን አሁን ደግሞ አንጋፋዋን የአማካይ እና የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቿን ሄለን ሰይፉን አስፈርሟል፡፡ በአዲስ አበባ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ስትጫወት የነበረችው አጥቂዋ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥም ከዚህ ቀደም ተጫውታ ያሳለፈች ሲሆን ዘንድሮ በአዳማ ከተማ ቆይታ ለማድረግ ክለቡን ተቀላቅላለች፡፡

ወጣቷ አማካይ ፋሲካ መስፍን ውሏን አራዝማለች፡፡ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በአዳማ ከተማ ስትጫወት የነበረችውና በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴን ስታደርግ እንዲሁም ቡድኑን በአምበልነት ስትመራ የነበረች ሲሆን ተጨማሪ አመትን በአዳማ ለመቆየት ኮንትራቷን አድሳለች፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ