​ቅዱስ ጊዮርጊስ አማኑኤል ገብረሚካኤልን አስፈረመ

አማኑኤል ገብረሚካኤል በይፋ ፈረሰኞቹን ተቀላቀለ፡፡

በሀገራችን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የተነሳ ዘንድሮ መቐለ በፕሪምየር ሊጉ መሳተፍ አጠራጣሪ በመሆኑ ፌድሬሽኑ ለዘንድሮው ዓመት ብቻ በሦስቱ የትግራይ ክልል ክለቦች ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች በሌላ ክለብ ገብተው መጫወት ይችላሉ ባለው መሰረት አጥቂው ፈረሰኞቹን ተቀላቅሏል፡፡

በዛሬው ዕለት ፊርማውን ካኖረ በኃላ የኮቪድ 19 ምርመራን ያደረገው ተጫዋቹ አራት ዓመታት ያሳለፈበት ክለብን ለቆ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ መጓዙ ተረጋግጧል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ