ከፍተኛ ሊግ | ቤንች ማጂ ቡና ተጨማሪ ተጫዋች ሲያስፈርም የነባሩን ውል አድሷል

ከሳምንት በፊት በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረመው የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ለ ቡድን ቤንች ማጂ ቡና ተከላካይ ሲያስፈርም የአጥቂውን ውል አድሷል።

ሂድር ሙስጣፋ የክለቡ አዲስ ፈራሚ ነው። የቀድሞው የጅማ አባ ቡና እና የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በኢትዮጵያ መድን የቆየ ሲሆን ቀጣይ ማረፊያው ቤንች ማጂ ሆኗል። ከአዲሱ ፈራሚ በተጨማሪ ባለፈው የወድድር ዓመት ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያሳይ የነበረው የቡድኑ አምበል ጌታሁን ማሙዬ ውሉን አድሷል።

ቤንች ማጂ በአጠቃላይ 10 ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአሰልጣኙን ጨምሮ የ15 ተጫዋቾችን ውል አድሷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ