ሀድያ ሆሳዕና አጥቂ አስፈረመ

ሚካኤል ጆርጅ ሀድያ ሆሳዕናን ተቀላቀለ፡፡

በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ የሚመሩት ሀድየ ሆሳዕናዎች በዝውውር ገበያው ከየትኛውም የፕሪምየር ሊግ ክለቦች በርካታ ተጫዋቾችን በማስፈረም የሚስተካከላቸው የሌለ ሲሆን አሁንም አጥቂው ሚካኤል ጆርጅን በይፋ ከአዳማ ከተማ ወደ ስብስባቸው አካተዋል፡፡ ከክለቡ ጋር ያለፉትን ሁለት ሳምንት ልምምድ ሲሰራ የሰነበተው የፊት መስመር ተሰላፊው ከዚህ ቀደም ለሙገር ሲሚንቶ፣ ሲዳማ ቡና፣ ደደቢት፣ ዳሽን ቢራ እንዲሁም በሁለት አጋጣሚዎች ያለፈውን ዓመት ጨምሮ ለአዳማ ከተማ የተጫወተ ሲሆን ከወር በፊት በአዳማ ለመቀጠል ቅድመ ስምምነት የፈፀመ ቢሆንም በመጨረሻም ማረፊያውን ሀድያ ሆሳዕና አድርጓል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ