ሰበታ ከተማ ከመስመር ተጫዋቹ ጋር በስምምነት ተለያየ

ሰበታ ከተማ ከመስመር አጥቂው አስቻለው ግርማ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ዘግይቶ ወደ ልምምድ የገባ ከመሆኑ ባሻገር የሰኞ እና ማክሰኞ መደበኛ ልምምዱን ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተገናኘ ሳይሰራ ትናንት ወደ ልምምድ የተመለሰው ሰበታ በዛሬው ዕለት ደግሞ ከመስመር አጥቂው ጋር ተለያይቷል፡፡ የቀድሞው የሱሉልታ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ተጫዋች የሆነው አስቻለው ግርማ በሰበታ ከተማ የተሰረዘውን የውድድር ዓመት በማሳለፍ ጥሩ ቆይታ ያደረገ ሲሆን የአንድ ዓመት ውል የሚቀረው ቢሆንም ይፋ ባልሆነ ምክንያት በጋራ ስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ