ከፍተኛ ሊግ | አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ስብስብ ይቀርባል

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ክለብ ሀያ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአምስት ነባሮችን ውልም አድሷል፡፡

በቅርቡ አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከርን የቀጠረው የከፍተኛ ሊጉ ክለብ አዲስ አበባ ከተማ በዝውውር መስኮቱ በርካታ አዳዲስ እና የተወሰኑ ነባር ተጫዋቾችን በመያዝ ወደ ሀዋሳ አምርቷል፡፡ በምድብ ለ የሚገኘው ክለቡ ሀያ ሶስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ጨምሮ አምስት ነባሮችን በድምሩ ሀያ ስምንት ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ግብ ጠባቂ የነበረው ሳምሶን አሰፋ፣ ሮቤል ግርማ እና ማራኪ ወርቁን የመሳሰሉ ተጫዋቾችንም በስብስቡ አካቷል፡፡


አዲስ ፈራሚዎች

ግብ ጠባቂዎች – ሳምሶን አሰፋ (ከድሬዳዋ)፣ ኮክ ኩዶስ (ከአካዳሚ)፣ ነብዩ ዳንኤል (ከስልጤ ወራቤ)

ተከላካዮች – ሮቤል ግርማ (ከጅማ አባቡና)፣ ዘሪሁን አንሼቦ (ከድሬዳዋ)፣ እያሱ ለገሰ (ከደደቢት)፣ ሳሙኤል አስፈሪ (ከየካ)፣ ፉአድ ጀሚል (ከወልድያ)፣ አቡበከር (ከገላን)፣ አሰጋኸኝ ጴጥሮስ (ከኮምቦልቻ)፣ ወንድማገኝ ሴራ (ከአርሲ ነገሌ)፣ ኤልያስ (ከታዳጊ ፕሮጀክት)


አማካዮች – ከድር አዩብ (ከድሬዳዋ)፣ አቤል ብርሀኑ (ከድሬዳዋ ፖሊስ)፣ ማራኪ ወርቁ (ከኢኮሥኮ)፣ የሺዋስ በለው (ፋሲል ከነማ)፣ ብዙዓየው ሰይፉ (ከሀላባ)፣ ምንተስኖት (ከታዳጊ ፕሮጀክት)፣ ሙከሪም (ከታዳጊ ፕሮጀክት)፣ አቡበከር ወንድሙ (ከሀላባ)፣ ሰዒድ ሰጠኝ (ከአውስኮድ)፣ ፍፁም ጥላሁን (ካፋ ቡና)


አጥቂዎች – ገዛኸኝ ባልጉዳ (ከሲዳማ ቡና)፣ ዘርዓይ ገብረሥላሴ (ከወሎ ኮምቦልቻ)

ውል ያደሱ

ዋኬኒ አዱኛ፣ ነብዩ ዱባ፣ ሙጃይድ መሀመድ፣ ተክሉ ተስፋዬ


© ሶከር ኢትዮጵያ