የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ውድድር የሚደረግብት ቦታ ተቀይሯል

በጅማ ስታዲየም እንዲደረግ ተወስኖ የነበረው የምድብ ሐ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የመጀመርያ ዙር ጨዋታዎች የቦታ ለውጥ እንደተደረገበት ታውቋል።

ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘው መረጃ መሠረት ጅማ ላይ ሊደረግ የነበረው ጨዋታ ወደ ድሬዳዋ ዞሯል። እንደ ምክንያትነት ደግሞ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ ላይ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎችን ስለሚያደርግ ነው ተብሏል።

ወደ ድሬዳዋ የዞረው የምድብ ሐ ውድድር ታኅሣሥ 27 እንዲጀምር ውሳኔ ሲተላለፍ በሀዋሳ እና ባቱ የሚደረጉት የምድብ ሀ እና ለ ውድድሮች ደግሞ ታኅሳስ 24 ይጀምራሉ ተብሏል።

በተያያዘ ዜና በውድድሩ የሚካፈሉ ክለቦች ክፍያ መፈፀም እንደሚገባቸው ሲነገር ክፍያ ያልፈፀሙት ግን በውድድሩ እንደማይሳተፉ ከፌዴሬሽኑ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በተያያዘ ዜና በሦስቱ ምድቦች ላይ ምንም አይነት መሸጋሸግ የሌለ ሲሆን ምናልባትም በተለያዩ ምክንያቶች በሚቀነሱት ቦታ መሸጋሸግ ሊኖር እንደሚችል ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ