ከፍተኛ ሊግ | ሺንሺቾ ከተማ አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአሰልጣኙን ውል አድሷል

ሺንሺቾ የአሰልጣኙን ውል ሲያድስ ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ ላይ የሚገኘው ሺንሺቾ ከተማ በሀዋሳ በሚደረገው ውድድር ላይ የሚሳተፍ ሲሆን የዋና አሰልጣኙ አስፋው መንገሻን ኮንትራት በማራዘም ዘጠኝ አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሞ አስራ ስድስት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት አድሷል፡፡

አዲስ የፈረሙ ተጫዋቾች ዳግም ዓለማየሁ (ተከላካይ ከአርባምንጭ ከተማ)፣ ሚሊዮን አበበ (ተከላካይ ከሾኔ ከተማ)፣ አዳነ አየለ (አማካይ ከኮልፌ ቀራኒዮ)፣ አሸናፊ ዋሎ (አማካይ ከሶዶ ከተማ)፣ ብርሃኑ ኤርዶሎ (አጥቂ ከደሴ ከተማ)፣ ናሆም አዕምሮ (አጥቂ ከሀምበሪቾ)፣ ማንደፍሮት ወልደጊዮርጊስ (አጥቂ ከየካ) ሲሆኑ አስራ ስድስት ነባሮች ደግሞ ኮንትራታቸውን አድሰዋል፡፡ ሆነልኝ ታሪኩ፣ ሆነልኝ ከበደ እና ቢንያም መንግስቱ ከተስፋ ቡድን ክለቡ ያሳደጋቸው ወጣቶች ናቸው፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ