ወላይታ ድቻ ከ ድሬዳዋ ከተማ – አሰላፍ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረው የድቻ እና ድሬዳዋ ጨዋታ የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።

አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ ቡድናቸው በፋሲል ከነማው ጨዋታ ከተጠቀመበት አሰላለፍ ግብጠባቂ ቦታ ላይ መክብብ ደገፉን በሰዒድ ሀብታሙ ቦታ ሲተኩ ከጉዳት እና ቅጣት የተመለሰው አናጋው ባደግ እና እዮብ በቀታም በአንተነህ ጉግሳ እና ፀጋዬ አበራ ቦታ በቀዳሚነት ጨዋታውን ጀምረዋል።

ጅማ አባ ጅፋር ላይ የመጀመሪያ ድሉን ያሳካው ድሬዳዋ ከተማ በዚያ ጨዋታ በቅጣት ያልተጠቀማቸው በረከት ሳሙኤል እና ዳንኤል ደምሴ ፣ ከጉዳት የተመለሰው ኩዌኩ አንዶህ እና ሙኸዲን ሙሳ እንዲሁም ሪችሞን ኦዶንጎን በመጀመሪያ አሰላለፉ ውስጥ ሲያካትት ከጅማ ጋር ተጎድቶ የወጣው ፍቃዱ ደነቀን ጨምሮ ዘነበ ከበደ ፣ አስጨናቂ ሉቃስ እና የፊት መስመር ጥምረቱ የነበሩት ጁኒያስ ናጂቡ እና ኢታሙና ኬይሙኒን ሳያካትት ጨዋውን ይጀምራል። በዚህም የአሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን ቡድን ባልተለመደ መልኩ በአሸናፊ ስብስቡ ላይ የአምስት ተጫዋቼች ለውጥ አድርጓል።

ወላይታ ድቻ

99 መክብብ ደገፉ
16 አናጋው ባደግ
12 ደጉ ደበበ
5 አዩብ በቀታ
27 መሳይ አገኘሁ
20 በረከት ወልዴ
8 እንድሪስ ሰይድ
28 አማኑኤል ተሾመ
4 ፀጋዬ ብርሀኑ
21 ቸርነት ጉግሳ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
12 ኩዌኩ አንዶህ
15 በረከት ሳሙኤል
14 ያሬድ ዘውድነህ
16 ምንያምር ጴጥሮስ
5 ዳንኤል ደምሴ
9 ኤልያስ ማሞ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
99 ሙኅዲን ሙሳ
22 ሪችሞንድ ኦዶንጎ

© ሶከር ኢትዮጵያ