ከፍተኛ ሊግ | ጌዴኦ ዲላ አስራ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሐ የሚገኘው ጌዴኦ ዲላ አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾች እና ዘጠኝ ነባሮችን አስፈርሟል፡፡

ክለቡ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን በማውጣት እዮብ ማለን ቀጥሮ ወደ ዝግጅት ከሳምንት በፊት የገባ ሲሆን አሰልጣኙም ውላቸው ተጠናቆ የነበሩ ነባር ዘጠኝ ተጫዋቾችን ኮንትራት በማደስ እንዲሁም አዳዲስ አስራ ሶስት ተጫዋቾችን በነበረበት ክፍት ቦታ ከተለያዩ ክለቦች በማስፈረም ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ክለቡ ከአዲስ እንዲሁም ደግሞ ነባር ተጫዋቾች በተጨማሪ አራት ወጣት ተጫዋቾችን ከሁለተኛው የክለቡ ቡድን ማሳደግ ችሏል፡፡

ክለቡ ያስፈረማቸው አዳዲስ ተጫዋቾች

ፍሰሀ ረዲ (ግብ ጠባቂ ከደብረ ብርሀን)

ተከላካዮች – አብነት አባተ (ከደብረ ብርሀን)፣ ደጀኔ ደምሴ (ከወልቂጤ ከተማ)፣ አሸብር ውሮ (ከአክሱም ከተማ)፣ አብርሀም ተስፋዬ (ከደብረ ብርሃን)

አማካዮች – ሙሉቀን ተስፋዬ (ከደብረ ብርሀን)፣ እስጢፋኖስ ግርማ (ከደብረ ብርሀን)፣ መልሰው መኮንን (ከደብረ ብርሀን)፣ ድልነሳው ሽታው (ከሶሎዳ ዓድዋ)፣ ፉአድ ተማም (ከጅማ አባ ቡና)

አጥቂዎች – ኩሴ ሞጮራ (ከስልጤ ወራቤ)፣ ሄኖክ ተረፈ (ከሀላባ ከተማ)፣ አላዛር ዘውዴ (ከሶሎዳ ዓድዋ)

ውል ያራዘሙ

ተካልኝ አየለ፣ አገኘሁ ብርሀኑ፣ ግርማ ፈይሳ፣ ፋሲል አበባየሁ፣ ዘመድኩን ሽርቆ፣ ምናሴ ወጋየሁ፣ ቢኒያም በቀለ፣ ሳሙኤል ቦጋለ እና ዘላለም አበራ

ከታችኛው የክለቡ ቡድን ያደጉ

መልካሙ አዳነ፣ መላሊኤል ብርሀኑ፣ ይሁን ገላጋይ እና ኃይሌ አዳነ


© ሶከር ኢትዮጵያ