ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በስድስተኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ታውቋል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ በኢትዮጵያ ቡና ከተሸነፈው ስብስባቸው የበርካታ ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ምንተስኖት አሎ፣ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ እና ጌቱ ኃይለማርያም በዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜ ጨዋታ የሚጀምሩ ሲሆን ቢያድግልኝ ኤልያስ፣ ያሬድ ሀሰን እና ታደለ መንገሻም በመጀመርያ አሰላለፍ ተካተዋል። ፋሲል ገብረሚካኤል፣ ዓለማየሁ ሙለታ፣ ፍፁም ገብረማርያም፣ ቡልቻ ሹራ፣ አዲሱ ተስፋዬ እና ኃይለሚካኤል አደፍርስ ደግሞ ከመጀመርያ አሰላለፍ የወጡ ናቸው።

አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው በበኩላቸው ከሀዋሳ ከተማ ነጥብ ከተጋራው የመጀመርያ አሰላለፍ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ሙሉቀን ታሪኩ እና ሮባ ወርቁን በብዙዓየሁ እንደሻው እና ጄይላን ከማል ምትክ ተጠቅመዋል።

ሁለቱ ቡድኖች ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ሰበታ ከተማ

1 ምንተስኖት አሎ
5 ጌቱ ኃይለማርያም
4 አንተነህ ተስፋዬ
12 ቢያድግልኝ ኤልያስ
24 ያሬድ ሀሰን
15 አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ
17 ታደለ መንገሻ
3 መስዑድ መሐመድ
8 ፉአድ ፈረጃ
10 ዳዊት እስጢፋኖስ
19 እስራኤል እሸቱ

ጅማ አባ ጅፋር

1 ጄኮ ፔንዜ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
14 ኤልያስ አታሮ
19 ተመስገን ደረሰ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
8 ሱራፌል አወል
22 ሳምሶን ቆልቻ
7 ሳዲቅ ሴቾ
10 ሙሉቀን ታሪኩ
27 ሮባ ወርቁ


© ሶከር ኢትዮጵያ