የሰዒድ ሀሰን ወቅታዊ ሁኔታ…

በረፋዱ ጨዋታ ከባድ ጉዳት አስተናግዶ ወደ ሆስፒታል ያመራው ሰዒድ ሀሰን ያለበትን ሁኔታ አጣርተናል።

በስድስተኛው ሳምንት የሊጉ መረሐ-ግብር ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን 2-0 ሲረታ የቀኝ መስመር ተከላካዩን በከባድ ጉዳት አጥቷል። በሲዳማ ቡናው አማኑኤል እንዳለ በተሰራበት ጥፋት ወዲያውኑ ወደ ዳኑ የህክምና ማዕከል የተወሰደው ሰዒድ አሁን ላይ በጥሩ ሁኔታ ላይ ቢሆንም ነገ የቀዶ ጥገና እንደሚደረግለት ከፋሲል ከነማው የህክምና ባለሙያ ሽመልስ ደሳለኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሰዒድ ያጋጠመው የአጥንት ስብራት ዓይነት Clavicle Fracture የሚባል ሲሆን ስብራቱ ከአንገቱ ወደ ትከሻው የሚሄደው አጥንት ላይ የደረሰ እንደሆነ ማወቅ ችለናል። እንደ ሽመልስ ደሳለኝ ገለፃ ከሆነ ሰዒድ ካልተራዘመ የህክምና ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ሰምተናል። ተጫዋቾቹ እርዳታ እየተደረገለት በሚገኝበት የህክምና ማዕከል በዶክተር ኤልያስ አህመድ አማካይነት ነገ የቀዶ ጥገናውን ያከናውናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ