የአሰልጣኞች አስተያየት | ሰበታ ከተማ 1-1 ጅማ አባ ጅፋር

ሱፐር ስፖርት የጅማ እና ሰበታ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ አሰልጣኞቹን እንዲህ አነጋግሯል።

አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ – ሰበታ ከታማ

ስለጨዋታው

“ጥሩ ነበር ሜዳ ላይ የነበረን እንቅስቃሴ። በአጠቃላይ ሙሉ ለሙሉ ጨዋታውን ተቆጣጥረነው ነበር። ከቅጣት ምት የተገኘ ኳስ አገቡ ከዛ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ሁሉም ተጫዋቾች ማለት ይቻላል ከኳስ ኋላ ሆነው ነበር ሲጫወቱ የነበሩት። ያንንም ለማስከፈት ብዙ ጥረት አድርገን ያገኘናቸውን ተደጋጋሚ እድሎች ወደ ጎል መቀየር አለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናል። በተረፈ ግን ተጫዋቾቼ ማድረግ ያለባቸውን ነገር በሙሉ አድርገዋል ብዬ ነው የማስበው።”

ኳስ በብዛት ቢቆጣጠሩም በጨዋታው አንድ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ብቻ ስለማድረጋቸውና ኳስ ይህንን ክፍተት ስለማሻሻል

“የዛሬው ጨዋታ ትንሽ የተለየ ነበር። እንደተመለከታችሁት ተጋጣሚያችን ሙሉ ለሙሉ ከኋላ ዘግቶ ነበር ሲጫወት የነበረው። ለማስከፈት ባደረግናቸው ጥረቶች ግብ አካባቢ ያገኘናቸውን ኳሶች ወደ ጎል መቀየር አለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናች። ከዚህ በተረፈ እድሎችን ላለማምከን ወደፊት ጠንካራ ስራ ከአጥቂዎቻችን ጋር መስራት ይጠበቅብናል ብዬ አስባለሁ።”

አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው – ጅማ አባ ጅፋር

ስለ ጨዋታው

“ውጤታችን ለማስጠበቅ ከፍተኛ ጥረት አድርገናል ፤ ልጆቹ የሚችሉትን ያህል መስዋዕትነት ከፍለዋል።ቡድናችን ጠቅጠቅ ብሎ በመከላከል እንዲሁም እንደ ቡድን በመከላከልና በማጥቃት ጥረት አድርገናል ፤ በውጤቱ ብዙም አልተከፋሁም።”

መከላከል ላይ ስለማተኮራቸው

“ፊት ላይ ዋነኛ አጥቂያችን ብዙዓየሁ ህመም አጋጥሞት ስለነበር ከመስመር አየተነሳን በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ እድሎችን መፍጠር ችለናል። ግብ ካስቆጠርንም በኃላ በመልሶ ማጥቃት ተጫውተናል ያም አዋጥቶን ነበር ፤ ነገርግን ግብ ቢቆጠርም እንደ አጠቃላይ ጥሩ ጨዋታ ነበር።”


© ሶከር ኢትዮጵያ