የሳምንቱ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የትኩረት ነጥቦች

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2013 የውድድር ዘመን ባለፈው ሳምንት መጀመሩር ይታወሳል። በዚህ ውድድር ላይ የተመለከትናቸውን ዋና ዋና ነጥቦችም በዚህ መልኩ አሰናድተናል። 

ቅሬታ የተሰማበት የኮቪድ 19 ምርመራ

በድሬዳዋ የሚገኘው የምድብ ሐ በኮቪድ ምርመራ ላይ ቅሬታ እያሰማ ይገኛል። የጉርምምታው ነገር ሁለት ሀሳብ ያለው ሲሆን በመጀመሪያው ጨዋታ ላይ የተጫዎቹች የኮቪድ ውጤት እጅጉን ዘግይቶ መድረሱ እንደዚሁም አወዳዳሪው ውጤቱ እጁ ላይ ሳይደርስ ወደ ሜዳ ማስገባቱ የቡድኖች ስነልቦና ላይ ጫና ስለያሚሳድር የህክምና እና የአወዳዳሪው አካል ከጨዋታ ቀደም ብሎ እንዲነገረን ማድረግ አለበት፤ ሌላኛው ደሞ ቡድኖች ማስመርመር የምንችለው ሀያ እና ሀያሁለት ተጫዎቾች ብቻ ነው የዚህ ቁጥር ማደግ አለበት። ከዚህ በተጨማሪ ለአገልግሎት የምን ከፍለው ክፍያ ደረሰኝ ይኖረው የሚል ጥያቄዎች አስተናግደዋል።

– ያልተገራው የኮቪድ 19 ጥንቃቄ ጉድለት

በ2013 የሀገር ውስጥ ውድድር በተመረጡ ቦታዎች ላይ ከመደረጋቸው አንፃር ቡድኖች ከጨዋታዎች 72 ሰዓት በፊት ምርመራ የቡድን አባላቶቻቸው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በማድረግ ውጤቱን ማሳወቅ እንደሚገባቸው ደንቡ ላይ በተቀመጠው መሠረት ክለቦች ተጫዋቾች በማስመርመር ውጤታቸውን ቢያሳውቁም ተጫዋቾቻቸውን በመቆጣጠር ረገድ ግን ክፍተቶች ይስተዋላል።

ምርመራ የተደረገላቸው የቡድኑ አባላቶች በተወሰነ ስፍራ ላይ ተለይተው እንዲቆዩ ቢጠበቅም የአንዳንድ ቡድን አባላቶች ከማረፊያ ቦታቸው ወጥተው በተለያዩ ስፍራዎች መታየት ቡድኑቹ ከማስመርመር በዘለለ በአባቶቹ ላይ ቀጣይነት ያለው ክትትል ማድረግ ላይ ያላቸውን የላላ አሰራር መፈተሽ ይኖርባቸዋል።

– የከፍተኛ ሊግ ቡድኖች መልካም ተግባር

በከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆኑት ደብረ ብርሃኖች በመጀመሪያው ጨዋታቸው ላይ የትጥቅ ጉድለት አጋጥሞቸው ውዝግብ ውስጥ በገቡበት ወቅት ተጋጣሚያቸው ለገጣፎ እርዳታ በማድረግ ወደ ጨዋታ እንዲገቡ እና ጨዋታው እንዲከናወን ያደረገው መልካም ተግባር ቡድኖች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚዳብር መልካም ተግባር ሆኖ አልፏል።

– የኮሚቴ ጥንካሬ

ምድብ ሀ ካሉት ሦስት ምድቦች በአንፃራዊነት በታቀደው እቅድ መሰረት እየተመራ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድሩ በራሱ ከፍ ያለ ጫና እና ውጥረት የተሞላበት መሆኑ ለኮሚቴዎች ከባድ ሲያደርግባቸው ይስተዋላል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን ደንብ በአግባቡ እና በጊዜ ውሳኔ የማያስተላልፉ በመሆኑ በቡድኖች ዙሪያ ቅራኒ ይሰማ ነበር። በዚህ ውድድር ዓመት በምድብ ሀ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ምንም አይነት ቅራኔ ሳያስተናግድ ቆራጥነት የተሞለበት ውሳኔ ሲስተላልፉ ታይተዋል። ይህን አይነቱን ድርጊት እስከ ውድድሩ መጨረሻ ድረስ የሚቀጥል ቢሆን መልካም ነው።

– በወጥነት የማይመራው የከፍተኛ ሊግ ውድድር

በታህሳስ 24 ይጀምራል ተብሎ እቅድ የወጣለት የከፍተኛ ሊግ ውድድር በእቅድ ያለመመራቱ ችግር ውድድሩን ለከፍተኛ ኪሳራ ይዳርጋል።

ቆራጥ የሆነ አመራር ሰጪነት የጎደለው ምድብ ሐ ደግሞ ታኃሣሥ 27 አንድ ጨዋታ ካደረገ በኋላ ቀጣይ ጨዋታ ጥር 1 የተደረገ ሲሆን ከአራት ቀን በኋላ ቀጣዮቹ ጨዋታ የመደረጉ አግባብነት ጥያቄ የሚነሳበት ነው።

– የውድድር ኳስ ማነስ

በሦስት የተለያዩ ቦታዎች ውድድሩን እያከናወነ የሚገኘው ከፍተኛ ሊግ አወዳሪው አካል ከሚያቀርባቸው መገልግጋያዎች አንዱ የሆነው ኳስ እጥረት የሚታይበት በመሆኑ አወዳዳሪው አካል ከኮሚቴዎች ጋር በመሆን ችግሩን መፍታት ይጠበቅበታል።

– እድለቢሱ ወልዲያ እና አይበገሬው ወራቤ

በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከከፍተኛ ሊግ ቡድኖች አንዱ የሆነውና በአሰልጣኝ ገብረዮሐንስ የሚመሩት ወልዲያዎች ቡድኑ ኳስን ለመቆጣጠር የማይቸገር በተደጋጋሚ የግብ እድሎችን የሚፈጥር ቢሆንም እንደ እድል ሆኖ ከጨዋታዎች ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዞ ለመውጣት ሳይችል ቀርቷል። ቡድኑ በሁለተኛው ሳምንት ጨዋታ ከተጋጣሚያቸው አንፃር በጨዋታው እንደነበራቸው የበላይነት ነጥብ ይዘው መውጣት ቢገባቸውም አሁንም ሙሉ ሶስት ነጥብ ማሳካት ሳይችሉ ቀርተዋል።

ስልጤ ወራቤ በ33ኛው ደቂቃ ለተጫዋቹ በረከት ቦጋለ በተሰጠበት የቀይ ካርድ ምክንያት ከተጋጣሚው በቁጥር ቢያንስም የወጣቱ አሰልጣኝ አብዱልወኪል አብዱልፈታህ ቡድን በጎደሎ ተጫውቶ አስደናቂ ትግል በማሳየት 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጋጣሚውን ማሸነፍ ችሏል።

-የጤና ጥበቃ መመሪያ የጣሰው ጨዋታ

በሃዋሳ እየተደረገ የሚገኘው የ2013 የከፍተኛ ሊግ ረቡዕ 10:00 ላይ ወላይታ ሶዶ ከ ሀላባ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ሶዶ ከተማ ሁለተኛ ጨዋታውን ከ48 ሰዓት ባነሰ ጊዜ አከናውኗል። የጤና ጥበቃ ሚኒስተር መመሪያ ቁጥር 4 በግልፅ እንዳስቀመጠው ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጨዋታው 48-72 ሰዓት በፊት የኮቪድ-19 ምርመራ ውጤትን ለአወዳዳሪው ማስገባታቸውን ማረጋገጥ ከጨዋታውም በኋላ ከ48-72 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዳግም የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ የሚል ቢሆንም ሳይተገበር ቀርቷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ