ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂ አስፈረመ

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂዋን ዮርዳኖስ ምዑዝን አስፈርሟል፡፡ 

በሀዋሳ እየተደረገ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የአሰልጣኝ መሠረት ማኔው ኢትዮ ኤሌክትሪክ እስከ አሁን በሊጉ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አራቱን አሸንፎ በአንዱ ብቻ ሽንፈትን አስተናግዷል፡፡ እስካሁን ውጤታማ ቢሆንም ከፍተኛ የአጥቂ ክፍተት በጉልህ የታየበት ክለቡ በትግራይ ክልል ባሉ ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾች የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈድሬሽን ባዘጋጀው አዲስ የዝውውር ደንብ መሠረት ወደ የትኛውም ክለብ ሄደው መፈረም ይችላሉ በሚለው ህግ መሠረት ከመቐለ 70 እንደርታ አጥቂዋ ዮርዳኖስ ምዑዙን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞዋ የደደቢት እና የመከላከያ ተጫዋች የኤሌክትሪክን የፊት መስመር ችግር ለመቅረፍ እስከ ዓመቱ መጨረሻ በቡድኑ ለመቆየት ፊርማዋን አኑራለች፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ