የጋቶች ፓኖም ቀጣይ ማረፊያ የት ይሆን?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በኢትዮጵያ ቡና በመቐሌ ሰባ እንድርታ እና በተለያዩ የውጭ ሀገራት የተጫወተው ግዙፉ አማካይ ጋቶች ፓኖም በቅርቡ ማረፊያው የት እንደሚሆን ለድረገፃችን ጠቆም አድርጓል። 

በኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ግዙፉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ቡናማዎቹን ከለቀቀ በኋላ ወደ ሩሲያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ አምርቶ ብዙም ቆይታን ሳያደርግ ወደ ሀገር ውስጥ ተመልሶ በመቐለ 70 እንደርታ ስድስት ወራትን ከቆየ በኋላ በግብፆቹ ኤል ጎውና እና ሀራስ ኤል ሁዳድ መጫወት ችሏል። በማስከተል ወደ ሳውዲ አረቢያ ዲቪዥን ሁለት (ሦስተኛ የሊግ እርከን) ክለብ አል-አንዋር ካመራ በኃላ በአሁኑ ወቅት ወደ ሀገሩ በመመለስ ክለብ አልባ በመሆን የተለያዩ ዕድሎችን እየጠበቀ ይገኛል። ሶከር ኢትዮጵያም ጋቶች ፓኖም አሁን ስለሚገኝበት ሁኔታ እና በቀጣይ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል ጠይቃ ይህን ብሏል።

” በአሁን በሀገሬ ነው ያለሁት። በዚህ አስራ አምስት ቀን ውስጥ ሲያልቅ ስሙን የማሳውቃችሁ ቢሆን የተሻለ ነው። ባላለቀ ነገር የክለቡንም ሆነ የሀገሩን ስም መጥቀሱ አስፈላጊ አይደለም። ዋናው ነገር በቅርብ ቀናት ውስጥ ወደ አንድ የውጭ ሀገር ሊግ ቡድን በቀጥታ ላመራ እችላለሁ። አብዛኛዎቹ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ ስለሆነ ነገሮች ይሳካል ብዬ አስባለው። ካልሆነ ግን አንደኛው ዙር ሲጠናቀቅ እዚሁ ሀገሬ ለአንዱ ክለብ ፊርማዬን እንደማኖር አስባለሁ። አጠቃላይ ግን ወደፊት የሚሆነውን የማሳውቅ ይሆናል።”


© ሶከር ኢትዮጵያ