አዳማ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በዘጠነኛው ሳምንት የመጨረሻ ቀን ላይ የተገናኙት አዳማ እና ድሬዳዋ ተከታዩን አሰላለፍ መርጠዋል።

አዳማ ከተማ የአምስት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ለዛሬው ጨዋታ ድርሷል። ግብ ጠባቂ ቦታ ላይ ኢብሳ አበበ የዳንኤል ተሾመን ቦታ ሲተካ ቀኝ መስመር ተከላካይ ቦታ ላይ በገጠመው በርካታ ጉዳት ታፈሰ ሰረካን በብሩክ ቦጋለ ለመለወጥ ተገዷል። ቡድኑ ባደረጋቸው ሌሎች ሦስት ለውጦች ሙጃይድ መሀመድ ፣ ፍሰሀ ቶማስ እና ጀሚል ያዕቆብን በበላይ አባይነህ ፣ ዘሪሁን ብርሀኑ እና አብዲሳ ጀማል ተቀይረዋል።

በርካታለውጦችን ለማድረግ የተገደዱት አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል ቡድናቸው ውስጥ መሻሻል እንዳለ ጠቅሰው ባላቸው አቅም የሚችሉትን ለማድረግ እየጣሩ እንደሆነ እና በዛሬው ጨዋታ ካለፈው የተለየ ነገር እንደማይኖር ተናግረዋል

በጅማ ከባድ ጊዜ እያሳለፍን ነው ያሉት አሰልጣኝ ፍሰሀ ጥዑመልሳን ሦስት ቅያሪዎችን ሲያደርጉ ፍቃዱ ወርቁ ፣ ሱራፌል ጌታቸው እና እንዳለ ከበደ ወጥተው ኤልያስ ማሞ፣ ኩዌኩ አንዶህ እና አስጨናቂ ሉቃስ ገብተዋል። አሰልጣኙ በየጨዋታዎቹ መሸነፍ ሲበዛ ጫና ውስጥ እንደገቡ ጠቅሰው የዛሬው ውጤት ካላማረ አንድ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።

በአሰላለፉ ሁለቱም ቡድኖች የማጥቃት ሀሳብ ኖሯቸው እንደሚገቡ የሚገመት ሲሆን ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ተፈሪ አለባቸው በመሐል ዳኝነት ይመራዋል።

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል :-

አዳማ ከተማ

50 ኢብሳ አበበ
19 ብሩክ ቦጋለ
20 ደስታ ጊቻሞ
44 ትዕግስቱ አበራ
6 እዮብ ማቲዮስ
4 ዘሪሁን ብርሀኑ
22 ደሳለኝ ደባሽ
9 በላይ አባይነህ
8 በቃሉ ገነነ
21 የኋላእሸት ፍቃዱ
10 አብዲሳ ጀማል

ድሬዳዋ ከተማ

30 ፍሬው ጌታሁን
2 ዘነበ ከበደ
21 ፍሬዘር ካሣ
6 ፍቃዱ ደነቀ
16 ምንያምር ጴጥሮስ
5 ዳንኤል ደምሴ
8 ሱራፌል ጌታቸው
17 አስቻለው ግርማ
11 እንዳለ ከበደ
99 ሙኅዲን ሙሳ
20 ጁንያስ ናንጄቦ


© ሶከር ኢትዮጵያ