የተጫዋቾች ማኅበር አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀ

መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል ባደረጉ ክለቦች ሲጫወቱ ቆይተው በአሁን ሰዓት ክለብ አልባ ሆነው በሚገኙ ተጫዋቾች ዙርያ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ማኅበሩ ጥያቄ አቅርቧል። 

በተፈጠረው ሀገራዊ ሁኔታ በትግራይ ክልል በተከሰተው ችግር ምክንያት ለሦስቱ ክለቦች እየተጫወቱ የሚገኙ ተጫዋቾች በአሁኑ ወቅት የዝውውር መስኮቱ በመዘጋቱ ምክንያት ክለብ ባለማግኘታቸው ራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር መቸገራቸውን የገለፀው ማኅበሩ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የሊግ ካምፓኒው በዚህ ጉዳይ በመወያየት ለችግሮቻቸው መፍትሔ እንዲፈልግላቸው አጭር ቀጠሮ እና አስቸኳይ መልስ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ