ኢትዮጵያውያን ዳኞች በቻን ውድድር ነገ ጨዋታ ይመራሉ

በካሜሩን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የቻን ውድድር ነገ የሚካሄደውን ጨዋታ ኢትዮጵያዊቷ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በመሐል ዳኝነት ትመራዋለች። 

ባሳለፍነው ቅዳሜ የተጀመረው የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር የምድብ ጨዋታዎች እየተካሄዱበት ሲሆን ቅዳሜ በሚደረገው የናሚቢያ እና ታንዛንያ ግጥሚያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታዎች ይጠናቀቃሉ። ምሽት 4:00 ላይ በሊምቤ ስታዲየም የሚደረገውን ይህን ጨዋታም ብቸኛዋ የውድድሩ ሴት የመሐል ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ የምትመራው ሲሆን በVAR ዳኝነት ወደ ስፍራው እንዳቀና የተነገረው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ በአራተኛ ዳኝነት በካፍ መመረጡን ለማወቅ ተችሏል።

በሀገር ውጥ ሊጎች በሚገኙ ተጫዋቾች የተዋቀሩ ብሔራዊ ቡድኖች ብቻ በሚሳተፉበት ይህ ውድድር ላይ ከተመረጡ 47 ዳኞች መካከል ሊዲያ ታፈሰ ብቸኛዋ ሴት ዳኛ መሆኗ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ