የሰበታ ከተማ እና ባህርዳር ከተማን ጨዋታ በመሩ ረዳት ዳኞች ላይ የእግድ ውሳኔ ተላለፈ

ሰበታ ከተማ በባህዳር ከተማ በተሸነፈበት ጨዋታ ስህተት ፈፅመዋል በተባሉ ዳኞች ላይ ቅጣት ተጣለባቸው፡፡ 

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስምንተኛ ሳምንት ጨዋታ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ባህር ዳር ከተማ እና ሰበታ ከተማን አገናኝቶ በባህር ዳር 4-1 አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ሰበታ ከተማዎች ያገቡት ጎል ከጨዋታ ውጪ ነው በሚል በረዳት ዳኞች የተሻሩ ሲሆን ሰበታዎችም በተደጋጋሚ እየተበደልን ነው በማለት የዳኝነት ስህተት ክስ በጨዋታው አስመዝግበው ነበር፡፡ ይህን አቤቱታ የመረመረው የሊግ ካምፓኒው የውድድር እና ስነ ስርአት ኮሚቴ ጨዋታውን በመሩት ሁለቱ ረዳት ዳኞች አሸብር ታፈሰ እና ባደታ ገብሬ ላይ የስድስት ወራት የእግድ ውሳኔ አስተላልፏል።

ደብዳቤው ይህን ይመስላል👇


© ሶከር ኢትዮጵያ