ወልቂጤ ከተማ ከ ፋሲል ከነማ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በዘጠነኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን የረፋድ ጨዋታ ላይ ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት አሰላለፍ ታውቋል።

በስምንተኛው ሳምንት አራፊ የነበረው ወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው በሰባተኛው ሳምንት አዳማ ከተማን ከረታው ስብስባቸው አማካዩ በኃይሉ ተሻገርን አሳርፈው በአጥቂው አህመድ ሁሴን በመተካት ለጨዋታው ቀርበዋል።

አሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ለጨዋታው የተለየ ዝግጅት እንዳላደረጉ ገልፀው “ተመልካቹ ነፃ እና አዝናኝ ጨዋታ ይመለከታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ ቡድናቸው በተመሳሳይ አዳማ ከተማን ካሸነፈበት ጨዋታ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ በማድረግ ሱራፌል ዳኛቸው እና ሳሙኤል ዮሐንስን በማሳረፍ ይሁን እንደሻው እና በረከት ደስታን በመጀመርያ አሰላለፍ አካተዋል።

አሰልጣኝ ሥዩም ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ሱራፌልን ተጠባባቂ አድርገው ይሁን እንደሻውን ያስጀመሩበት ምክንያት ታክቲካዊ እንደሆነና ባለፈው ሳምንት ያደረጉት ቅያሪ ያመጣው ለውጥን ከግምት በማስገባት እንደሆነ ገልፀዋል። በተጨማሪም ከጅማ ጨዋታዎች 100% ድል ለማሳካት መምጣታቸውንና እስካሁን ገሚሱን ስለማሳካታቸው ተናግረዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ሄኖክ አክሊሉ በመሐል ዳኝነት ይመራዋል።

የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ይህንን ይመስላል:-

ወልቂጤ ከተማ

1 ጀማል ጣሰው
12 ተስፋዬ ነጋሽ
30 ቶማስ ስምረቱ
19 ዳግም ንጉሤ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
14 አብዱልከሪም ወርቁ
13 ፍሬው ሰለሞን
20 ያሬድ ታደሰ
26 ሄኖክ አየለ
10 አህመድ ሁሴን

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 እንየው ካሣሁን
5 ከድር ኩሊባሊ
16 ያሬድ ባየህ
21 አምሳሉ ጥላሁን
14 ሀብታሙ ተከስተ
8 ይሁን እንደሻው
17 በዛብህ መለዮ
7 በረከት ደስታ
19 ሽመክት ጉግሳ
26 ሙጂብ ቃሲም


© ሶከር ኢትዮጵያ