ሀዋሳ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

በጉጉት የሚጠበቀው የዘጠነኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ተጋጣሚዎች አሰላለፍ ታውቋል።

ለዋንጫ ከሚፎካከር ቡድን ጋር ቢገጥሙም የተለየ ዝግጅት እንዳላረጉ እና በሰሞኑ አቀራረባቸው እንስደሚቀጥሉ የተናገሩት አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት እንዳሉትም ቡድናቸው ሲዳማ ቡናን በረታበት የመጨረሻ ጨዋታ ከተጠቀሙት የመጀመሪያ አሰላለፍ ላይ ምንም ለውጥ ሳያደርጉ ጨዋታውን ጀምረዋል።

የደመወዝ በወቅቱ አለመከፈል በቡድኑ ተነሳሽነት ላይ ተፅዕኖ ሊኖረው እንደሚች ሆኖም ከተጫዋቾቻቸው ጋር ተነጋግረው ውጤት ይዘው ለመውጣት እንደተዘጋጁ የገለፁት አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከቅጣት የተመለሰላቸውን ግብ ጠባቂው መሀመድ ሙንታሪን በደረጄ ዓለሙ ተክተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ባደረጉት አንድ ለውጥ ደግሞ መድሀኔ ብርሀኔ በአዲስ ህንፃ ምትክ ጨዋታውን ጀምሯል።

ተጠባቂውን ጨዋታ አርቢትር ዮናስ ማርቅስ በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል

የሁለቱ ቡድኖች የዛሬ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ሀዋሳ ከተማ

1 ሜንሳህ ሶሆሆ
7 ዳንኤል ደርቤ
4 ምኞት ደበበ
26 ላውረንስ ላርቴ
12 ደስታ ዮሐንስ
18 ዳዊት ታደሰ
3 ኤፍሬም ዘካርያስ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ሀዲያ ሆሳዕና

77 መሀመድ ሙንታሪ
2 ሱሌይማን ሀሚድ
5 አይዛክ ኢሴንዴ
3 ቴዎድሮስ በቀለ
17 ሄኖክ አርፊጮ
21 ተስፋዬ አለባቸው
14 መድኃኔ ብርሀኔ
10 አማኑኤል ጎበና
22 ቢስማርክ አፒያ
20 ሳሊፉ ፎፋና
12 ዳዋ ሆቴሳ


© ሶከር ኢትዮጵያ